በእነ ዶክተር ደብረፅዮን የክስ መዝገብ ከተከሰሱ 62 ተከሳሾች መካከል 19ኙ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ በጽሑፍ እንዲደርሳቸው ተደረገ፡፡

188

በእነ ዶክተር ደብረፅዮን የክስ መዝገብ ከተከሰሱ 62 ተከሳሾች መካከል 19ኙ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ በጽሑፍ እንዲደርሳቸው ተደረገ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 26/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በእነ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የክስ መዝገብ ከተከሱ 62 ተከሳሾች መካከል 19ኙ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ በጽሑፍ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

በዚህ መሠረትም አቶ ስብሐት ነጋ እና ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ጨምሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ 19 ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ በጽሑፍ ደርሷቸዋል።

ሁለት ተከሳሾች ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ ሲሰጥ ስማቸው ባለመካተቱ ምክንያት ፍርድ ቤት መቅረብ አለመቻላቸው ተመላክቷል፡፡

እንደ ፋብኮ ዘገባ ፖሊስ በችሎቱ ያልተገኙት ዶክተር ደብረፅዮንን ጨምሮ 41 ተከሳሾችን ለማቅረብ አሁን ላይ በትግራይ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ እንዳስቸገረው አብራርቷል።
በችሎቱ ሰፊ የሰነድ ማስረጃ ቀርቧል፡፡ ፖሊስ ያላቀረበው የተንቀሳቃሽ ምሥል ማስረጃ እንዳለውም ተገልጿል።

ፍርድ ቤቱ ክሱን ለማንበብ እና ያልቀረቡ ሁለት ተከሳሾች እንዲቀርቡ ለነሐሴ 11/2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየአማራ ፋኖ ሀገር አፍራሹን አሸባሪ ቡድን አከርካሪ ለመስበር ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከሁሉም ክልል ከተውጣጡ ልዩ ኅይሎችና ከአማራ ሚሊሻ ጋር በመኾን አኩሪ ድሎችን እያስመዘገበ ነው፡፡
Next articleግንባር በመሰለፍ የህይወት መሰዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መኾናቸውን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሥራ ኀላፊዎች እና ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡