
ባሕር ዳር፡ መስከረም 14/2012 ዓ.ም (አብመድ) ‹ስታርፊሽ› የሚል ቅጽል መጠሪያ የተሰጠው ግዙፉ የቤጂንግ ‹ዳክሲንግ› ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሥራ መጀመሩ ተሰምቷል፡፡
ከ11 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጭ የተደረገበት አዲሱ የአውሮፕላን ማረፊያ በዓለማችን በአየር ትራፊክ መጨናነቅ ሁለተኛ ለሆነው የቤጅንግ ነባሩ አውሮፕላን ማረፊያ እፎይታ የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡
የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ዢን ፒንግ ዛሬ አውሮፕላን ማረፊያውን በይፋ ሥራ አስጀምረዋል፡፡ የአውሮፕላን ማረፊያው ቻይና 70ኛ ዓመት ክብረ በዓሏን በምትዘክርበት ዋዜማ መመረቁም ነው የተገለጸው፡፡
‹‹ዳክሲንግ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ›› የተባለው የቤጂንጉ አውሮፕላን ማረፊያ 700 ሺህ ስኩየር ሜትር (98 የእግር ኳስ ሜዳዎችን) ያህል ስፋት እንዳለው ተነግሯል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ
በአብርሃም በዕውቀት