“የክተት ጥሪውን በመቀበል በተጠንቀቅ ላይ እንገኛለን ” የቃብትያ ሁመራ ወረዳ ነዋሪዎች

219

“የክተት ጥሪውን በመቀበል በተጠንቀቅ ላይ እንገኛለን ” የቃብትያ ሁመራ ወረዳ ነዋሪዎች

ባሕር ዳር: ሐምሌ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ)ማንነታችንን በመጠየቃችን በአሸባሪው ትህነግ ስንታፈን፣ ስንገደል ኖረናል ያሉት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የቃብትያ ሁመራ ወረዳ ነዋሪዎች አሸባሪውን የትህነግ ቡድን እስከመጨረሻው ለመደምሰስ ቆርጠን ተነስተናል፤ በተጠንቀቅም ላይ እንገኛለን ብለዋል ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ።

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የቃብትያ ሁመራ ወረዳ አድህርድ ከተማ ነዋሪ ቄስ ሰረበ ማሞ “ሀገር ስትኖር ነው ሃይማኖት የሚኖረን” ብለዋል።

የአማራ ሕዝብ በዘር ወቅት ገበሬ በበዓል ቀን ቄስ በጦር ጊዜ ጀግና ነው ያሉት ቄስ ሰረበ እርሳቸውም የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ሌላው የከተማዋ ነዋሪ እና በንግድ ሥራ የሚተዳደረው ወጣት ልዑል ከሰተ “የክተት ጥሪውን ተቀብየ ስልጠናን እየወሰድኩ እገኛለሁ፤ ጁንታው ሳይደመሰስ እንቅልፍ አይኖረኝም” ብሏል።

ጣሂር ሙሃመድ ፋራህ የተባሉ የከተማዋ ነዋሪ “ማይካድራ ላይ የተፈጸመብንን ግፍ አንረሳም፤ ለአማራ ጦርነት ሰርጉ መሆኑን በተግባር እናረጋግጣለን” ብለዋል።

ወልቃይት ጠገዴ የጁንታው መቀበሪያ ትሆናለች ያሉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳዳሪ አሸተ ደምለው ሁሉም በህልውና ዘመቻው እንዲሳተፍ እና ማንነቱን አስጠብቆ እንዲዘልቅ የዞኑ አስተዳዳሪ አሳስበዋል።

በሰልፉ ላይ መከላከያ ሠራዊት የሉዓላዊነታችን ምልክት ነው፣ ከልዩ ኃይል፣ ከሚሊሻ እና ከፍኖ ጎን ነን፣ አንድነታችንን ጠብቀን በህልውናችን ላይ የተጋረጠውን ጠላት እናጠፋለን፣ የሕወሓት ጁንታ ቡድን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠላት ነው የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል።

በሰልፉ ላይ የአማራ ክልል ፓሊስ ማርሽ ባንድ ወኔ ቀስቃሽ ጣዕመ ዜማዎችን አሠምቷል፡፡

ዘጋቢ፡-ያየህ ፈንቴ- ከአድህርድ ከተማ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleለክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና ለቀድሞው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ በስማቸው ጎዳና የመሰየም ሥነ ሥርዓት በጎንደር ከተማ ተካሄደ።
Next articleየቀድሞ የኢትዮጵያ የአየር ወለድ ሠራዊት አባላት አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ለመደምሰስ መንግሥት የሚሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ።