በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 100 ሺህ ዶላር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ተሰበሰበ፡፡

107
በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 100 ሺህ ዶላር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ተሰበሰበ፡፡
 
ባሕር ዳር: ሐምሌ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ለመጀመሪያ ጊዜ በ24 ሰዓት ውስጥ 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ለመሰብሰብ መቻሉን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታወቁ።
 
አምባሳደሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው “በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አዲስ ታሪክ ተጻፈ!” በማለት ገልጸዋል፡፡
 
ዲያስፖራው ለህዳሴ ግድብ ድጋፍ በማድረግ ከ60 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለመጀመሪያ ጊዜ ብርሃን እንዲያይ ምክንያት እየሆነ ነው ያሉት አምባሳደር ፍጹም “ህይወት ራሷ ስጦታ ናት! ከስጦታችን ለመስጠት ላበቃን ፈጣሪ ምስጋና ይግባው! እጅግ እናመሰግናለን” ሲሉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራን አመስግነዋል።
 
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleበደቡብ ወሎ ዞን አምሐራ ሳይንት ወረዳ የክተት ጥሪውን ተቀብለው ወደ ዘመቻ ለሚሄዱ ወጣቶች አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡
Next articleበበይነ መረብና በሞባይል ባንኪንግ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡