
በደቡብ ወሎ ዞን አምሐራ ሳይንት ወረዳ የክተት ጥሪውን ተቀብለው ወደ ዘመቻ ለሚሄዱ ወጣቶች አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡
ባሕር ዳር: ሐምሌ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት ለህልውና ዘመቻው የክተት ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ የክልሉን መንግሥት የክተት ጥሪ የተቀበሉት የአምሐራ ሳይንት ወረዳ የቁርጥ ቀን ልጆች ወደ ህልውና ዘመቻው ሲሄዱ የአጅባር ከተማ ሕዝብ አሸኛኘት አድርጎላቸዋል፡፡ የከተማዋ ሕዝብ ስንቅ በማቀበል ነው የሸኛቸው፡፡
የሃይማኖት አባቶችም ለዘማቾቹ ስጦታ በመስጠትና በሰላም ደርሰው በድል እንዲመለሱ በጸሎት ሸኝተዋቸዋል፡፡
የአጅባር ከተማ ነዋሪዎች በህልውና ዘመቻው አስፈላጊውን ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ በግንባር በመሰለፍ አብረዋቸው እንደሚሆኑ ገልጸውላቸውዋል፡፡ በወረዳው እስካሁን ለሕልውና ዘመቻ ካቀኑት በተጨማሪ የተተኪ ኃይል ሥልጠናና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑም ታውቋል፡፡
የአጅባር ከተማ ሕዝብ የሕልውና ዘመቻውን ለመቀላቀል ጉዞ ለጀመሩ ወጣቶች ላደረገው ደማቅ አሸኛኘት እና ላለው ድጋፍ የወረዳው አስተዳዳር ምስጋና አቅርቧል ፡፡

መረጃውን ያደረሰን የአምሐራ ሳይንት ወረዳ ኮምዩኒኬሽን ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
