
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 2 ሺህ 732 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡
ባሕር ዳር: ሐምሌ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ወሎ ዩኒቨርስቲው ዛሬ ካስመረቃቸው 2 ሺህ 732 ተማሪዎች ውስጥ 949 ሴቶች ናቸው። ዩኒቨርሲቲው በሁለት ኮሌጆች በ22 ቅድመ ምረቃ እና በ5 ድህረ ምረቃ መርኃግብር ነው ተማሪዎቹን ያስመረቀው።
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ አለሙ ሰሜ (ዶክተር ) ተመራቂ ተማሪዎች በግቢ ቆይታቸው ከቀሰሙት እውቀት ባሻገር በሀገር ፍቅር ስሜት ሀገራቸውን እንዲያገለግሉም አሳስበዋል።
የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት አፀደ ተፈራ (ዶክተር) ተመራቂ ተማሪዎች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ለሀገራቸው ሁለንተናዊ እድገት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

በ13ኛው ዙር የወሎ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች መረቃ መርኃግብር ላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪና የቀድሞው የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት አባተ ጌታሁንን (ዶክተር ) ጨምሮ የደሴ ከተማ ከንቲባ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡- ቤተልሔም ሰለሞን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
