
የአፋር ክልል ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት በመቆም በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ሕብረቱን እንዲያጠናክር ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ አሳሰቡ።
ባሕር ዳር:ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድሩ ከክልሉ የተለያዩ አደረጃጀት የተውጣጡ ሴቶች የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ በሚኖራቸው ሚና ላይ ዛሬ በሠመራ ከተማ በመከሩበት ወቅት እንዳሉት፤ ጁንታው የአፋር ክልል ወረራ የአፋርን ህዝብ በጉልበት በመጨፍለቅ “ታላቋ የትግራይ ሪፐብሊክን” ለመመስረት የነበረውን የቆየ ድብቅ አጀንዳ ግልጽ ያወጣ የእብሪት ተግባር ነው።
የአፋር ክልል ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት በመቆምበአሸባሪው የሕወሓት ቡድን የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ህብረቱንእንዲያጠናክርም አሳስበዋል።
አሸባሪው ሕወሓት በክልሉ ፈንቲ-ረሱ ዞን በፈጸመው ወረራ ማየት የተሳናቸው፣ አቅመደካሞችን፣ ነፍሰ ጡር እና ጨቅላ ሕጻናት በግፍ ጨፍጭፏል።
“በዚህና ታሪክ ይቅር በማይለው ክብረ-ነክ ተግባሮቹ የሽብር ቡድኑና የእሱ ጋሻ-ጃግሬዎች የአፋር ሕዝብ ታሪካዊና ቁጥር አንድ ጠላቶች ናቸው” ብለዋል።
የአፋር ሕዝብ ይህን ጠላቱን አሳፍሮ ወደመጣበት በመመለስ ዘመን ተሻጋሪ አኩሪ ታሪክ ማስመዝገብ የዚህ ትውልድ አደራ መሆኑንም ገልጸዋል።
ይህን ታሪካዊ አደራ በብቃት ለመወጣት ሴቶችን ጨምሮ የክልሉ ወጣቶች፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የክልሉ ልዩ ኀይል አባላት በታላቅ ግዳጅ ውስጥ መሆናቸውን አቶ አወል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
