
‹‹እናት ከመጨረሻው ምጥ በኋላ አዲስ ልጇን አይታ እንደምትደሰተው ሁሉ ኢትዮጵያም ከገጠማት ከባድ አደጋ በድል ወጥታ ኢትዮጵያዊነት አሸናፊ ይሆናል›› አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተቀብሏል፡፡ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ስለ ኢትዮጵያዊነት፣ ስለፍቅር፣ ስለ አባይ፣ ስለ አድዋ ጀግኞች እና ስለአንድነት ያቀነቀነ የሀገር ባለውለታ ድምጻዊ ነው፡፡
አርቲስቱ ለተመራቂዎች መልዕክት አስተላልፏል፡፡ አርቲስት ቴዎድሮስ እንዳለው ሀገሪቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ የገባችበት አጣብቂኝ ፈታኝ ቢኾንም ‹‹እናት ከመጨረሻው ምጥ በኋላ አዲስ ልጇን አይታ እንደምትደሰተው ሁሉ ኢትዮጵያም ከገጠማት ከባድ አደጋ በድል ወጥታ ኢትዮጵያዊነት አሸናፊ ይሆናል››ነው ያለው፡፡
ባለፍት ዓመታት ሀገሪቱ ለገባችበት ችግር የዳረጋት የጎሳ ፖለቲካ ተወልዶ፣ አድጎ፣ አርጅቶ እና በስብሶ ተፈጥሯዊ ሞቱን ሞቷል ብሏል አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን፡፡
ከዚህ በኋላ ወጣቶች በጎሳ እና በሃይማኖት ልዩት ሳይፈጥሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት እንዲቆሙ አሳስቧል፡፡ ሰላም እና ፍትሕ የሰፈነባት ኢትዮጵያ ማየት የወጣቱ ራዕይ ሊሆን እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፏል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
