
የሰሜን ጎንደር ዞን የሃይማኖት አባቶች ከዞን የሥራ ኀላፊዎች ጋር በወቅታዊ የህልውና ዘመቻ ላይ ተወያዩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሃይማኖት አባቶቹ በህልውና ዘመቻው እስካሁን በሰሯቸውና ወደፊት በሚያከናውኗቸው ተግባራቶች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ አሸባሪው ትህነግ ለ27 ዓመታት በእምነት ተቋማት፣ በሃይማኖት አባቶች እና በምዕመኑ ላይ በደል ሲፈፅም የኖረ ቡድን መሆኑና አሁንም የእምነት ተቋማትን ምሽግ እና የጦር መሳሪያ ማከማቻ እያደረገ ያለ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ለማጥፋት የተነሳ የክፋት ቡድን መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
ይህን ኀይል እስከመጨረሻው ለማስወገድ የክልሉ መንግሥት የክተት ጥሪ ካስተላለፈ ጊዜ ጀምሮ ሁሉም በየዘርፉ ጁንታውን ለመደምሰስ አስተዋጽዖ እያደረገ እንደሚገኝ ተነስቷል፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን የሃይማኖት አባቶችም የህልውና ዘመቻውን ተቀላቅለው የራሳቸውን አሻራ ማሳረፍ እንደሚገባቸው በውይይቱ ተመላክቷል፡፡
የሃይማኖት አባቶች ከሕዝብ መካከል የሚኖሩና ለጠላት የሚሰሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በመምከርና ማኅበረሰቡ በሀሰት ፕሮፖጋንዳ እንዳይሸበር የማድረግ ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡
በመስጊዶችና አብያተ ክርስቲያናት ጁንታው ተላላኪዎቹን ተማሪ፣ ነዳያን፣ መናኝ እያስመሰለ አሰማርቷል፤ እነዚህን ተላላኪዎችና ሰላዮች ለመያዝ በእምነት ተቋማትም ለአብነት ትምህርት ተማሪዎች የደረት ባጅ ተዘጋጅቶ እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ መሆኑንና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሃይማኖት አባቶች በውይይቱ አረጋግጠዋል፡፡
በመጨረሻም የሃይማኖት አባቶች ለህልውና ዘመቻው እስካሁን ካበረከቱት በተጨማሪ በየአብያተ ክርስቲያናቱና በየመስጊዱ ገንዘብ ለማሰባሰብ እና ደሞዝ ያላቸው የሃይማኖት አባቶች ከደሞዛቸው ቀንሰው ለህልውና ዘመቻው ሊሰጡ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
ዘጋቢ:–አድኖ ማርቆስ–ከደባርቅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
