የኪነ-ጥበቡ ማኅበረሰብ ሀገር የማዳን ዘመቻውን በሙያው እንዲያግዝ የመከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ጥሪ አቀረቡ።

376

የኪነ-ጥበቡ ማኅበረሰብ ሀገር የማዳን ዘመቻውን በሙያው እንዲያግዝ የመከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ጥሪ አቀረቡ።

ባሕር ዳር: ሐምሌ 23/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ለሀገር ህልውና ያላቸው ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ብዙነሽ መሰረትን ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችና ወታደራዊ መኮንኖች እንዲሁም የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ሙያተኞች በተገኙበት ተካሂዷል።

የመከላከያ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያውያን በየዘመናቱ የገጠሟቸውን የውጭ ወራሪዎችና ውስጥ ጸረ-ሰላም ኀይሎች በድል ሲመክቱ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

የመከላከያ ሠራዊቱ የሕወሓት አሸባሪ ቡድንን ጨምሮ ሌሎች ጠላቶችን ለመመከት ዝግጁ መሆኑንም አስታውቀዋል። አሁናዊ ሁኔታው የሥነ ልቦና ጦርነት እንደመሆኑ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በተናጠልም ኾነ በቡድን ሆነው ሀገር የማዳን ዘመቻውን የሚያግዙ የፈጠራ ሥራዎችን እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ተወካይ ብርጋዴር ጀኔራል አስፋው ማመጫ በበኩላቸው ኪነ-ጥበብና መከላከያ የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፤ “የመከላከያ ሠራዊቱ ለኪነ-ጥበብ ትልቅ ሥራ ሠርቷል፤ ስመ-ጥር የጥበብ ሰዎችንም አፍርቶ ለሀገር አብቅቷል” ብለዋል።

ኢትዮጵያ በየዘመናቱ የገጠሟት ጠላቶች እንዲወድቁና ሀገር ድል እንድትነሳ ኪነ-ጥበብ ትልቅ ሚና እንደነበረው አውስተው ጀግንነት፣ አርበኝነት፣ የሀገር ፍቅርና አሸናፊነት በኢትዮጵያውያን ዘንድ ባሕል እንዲሆን ኪነ- ጥበብ በጎ ሚና ማበርከቱንም ብርጋዴር ጀኔራል አስፋው ተናግረዋል።

በሶማሊያ ወረራ ወቅት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የነበራቸውን ጉልህ ሚና ለአብነት ጠቅሰው በቀጣይም ሀገር ለማዳን በሚደረገው ትግል በመሳተፍ ደማቅ ታሪክ እንዲጽፉ አደራ ብለዋል።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒትር ዴኤታ ወይዘሮ ብዙነሽ መሰረት፤ መድረኩ የኪነ-ጥበብ ኅህበረሰቡ ለሠራዊቱ ያለውን ድጋፍ ለማሳየት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ኪነ ጥብብ በደስታ ብቻ ሳይሆን በችግር ጊዜም እስከ ጦር ሜዳ ድረስ በመሄድ ጠላትን ደል ለመንሳት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

በዚህም የኪነ-ጥበቡ ማኅበረሰብ ኮሚቴ አዋቅሮና የአጭር፣በመካከለኛና ረዥም ጊዜ እቅድ ይዞ ወደ ሥራ መግባቱን መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቶኪዮ ኦሎምፒክ በተገኘው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
Next article“በጠላቶቻችን የተደቀነብን የህልውና አደጋ በጣጥሰን ለመሻገር ሁሉም ዜጋ ከመቼውም ጊዜ በላይ መተባበር ፣ ጠላት ከሚነዛው አሉባልታ ወሬ ራስን መጠበቅ ፣ አንድነታችንን እና ሕብረታችንን ማጠናከር ወቅቱ የሚጠይቀው ዐብይ ጉዳይ ነው” መከላከያ ሚኒስቴር