ሰባት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ወርቅና የዉጪ ሀገራት ገንዘቦች ተያዙ፡፡

228

ባሕር ዳር፡ መስከረም 14/2012 ዓ.ም (አብመድ) በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የቶጎ ጫሌ መቅርጫ ጣቢያ 7 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ 5ኪ.ግ ወርቅና የዉጪ አገር ገኝዘቦችን መያዙ ተገለጸ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በማኅበራዊ ገጹ እንዳስታወቀው በቀን መስከረም 13 ቀን 2012ዓ.ም ከሌሊቱ 9፡00 አካባቢ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ጫት በጫነ አይሱዚ የቶጎ ጫሌ ፈታሾች ባደረጉት ጥረትና ጠንካራ ፍተሻ 5 ኪ.ግ ጥፍጥፍ ወርቅ፣ 175 ሺህ 584 የሳውዲ ሪያል እና 7 ሺህ 155 ድርሀም በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ለቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ጠንካራ ክትትልና የተመዘገበ ውጤት ምሥጋና አቅርቧል፡፡ የተያዘዉ ወርቅና ገንዘብም ለብሔራዊ ባንክ ገቢ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

Previous articleባርሴሎና በጠባብ ውጤት ቢያሸንፍም ሊዮኔል ሜሲን በጉዳት አጥቷል፡፡
Next articleበሀገሪቱ የቫይረሱ ስርጭት 4 ነጥብ 9 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡