
የክተት ጥሪው ህልውናን የማስቀጠል አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን በመገንዘብ ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 23/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ነዋሪዎቹ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡ የከተማው ከንቲባ ከማል መሐመድ ኢንጅነር (ዶ.ር) የህልውና ዘመቻው ኢትዮጵያን ማዳን መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በከተማው ለጁንታው እኩይ ዓላማ ተባባሪ የሚሆን ግለሰብም ሆነ ተቋም ከተገኘ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት አሳስበዋል፡፡
የአማራ ሕዝብ ጀግንነቱን በዓድዋ ተራሮችና በማይጨው ማስመስከሩን ከንቲባው አውስተዋል፤ ሽብርተኛው ትህነግ አማራን በጠላትነት ፈርጆ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እያደረገ ያለውን ከንቱ ሙከራ ከአያቶቻችን በወረስነው ወኔ እናከሽፈዋለን ነው ያሉት፡፡
ነዋሪው ለሠራዊቱ ስንቅ ከማዘጋጀት ጀምሮ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ ነዋሪዎች የክተት ጥሪው ህልውናን የማስቀጠል አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን በመገንዘብ ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አሊ ይመር – ከኮምቦልቻ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
