ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኀን የመልስ ምት የሚሰጥ እና ሴራውን የሚያጋልጥ ጠንካራ የመገናኛ ብዙኀን መገንባት እንደሚያስፈልግ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኀን ውስጥ የሚሠሩ ጋዜጠኞች ተናገሩ፡፡

351

ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኀን የመልስ ምት የሚሰጥ እና ሴራውን የሚያጋልጥ ጠንካራ የመገናኛ ብዙኀን መገንባት እንደሚያስፈልግ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኀን ውስጥ የሚሠሩ ጋዜጠኞች ተናገሩ፡፡

ባሕር ዳር:ሐምሌ 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬም እንደ ትናንቱ መልኩን ቀይረዉ በአፍሪካዊያን ላይ የባርነት ቀንበር መጫን የሚናፍቁ ምዕራባዊያን በኢትዮጵያ ላይ ተጽዕኖ እየፈጠሩ ያሉት ህልማቸዉ እንዳይሳካ አፍሪካዊያንን ታጀግናለች በሚል እንደኾነ በዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኀን የሚሠሩ ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

መንግሥት ምዕራባዊያን ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱት የሀሰት የመረጃ ጦርነት የተደራጀ እና መንግሥታዊ ድጋፍ ያለበት ዘመቻ እንደኾነ መረዳት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ጋዜጠኞቹ እንዳሉት መንግሥት ይህን ተረድቶ ችግሩን መቋቋም የሚችሉ እና ችግሮችን የሚያጋልጡ የሚዲያ ተቋማትን መገንባት እና ከተቋማቱ ጋር ተናቦ መሥራት ላይ የቀጣይ የቤት ሥራዉ መኾን አለበት፡፡

ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ የነበራቸዉ ዓለም አቀፍ ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ምዕራባዊያን አሁንም ቢኾን ስለኢትዮጵያ እና አፍሪካዊያን ያላቸዉ አመለካከት በንቀት የተቃኜ እንደኾነ ነው የነገሩን፡፡

ጋዜጠኞቹ ምዕራባውያን የሚሠሩት ሥራ ዛሬም እንደ ትላንቱ መልኩን ቀይረዉ በአፍሪካዊያን ላይ የባርነት ቀንበር መጫን እንደሚፈልጉ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ምዕራባዊያን ሚዲያዎች ኢትዮጵያ ላይ የከፈቱት የመረጃ ጦርነት ቅንጅት ያለው እና በገንዘብ የተደገፈ እንደኾነ የሚናገሩት ጋዜጠኞቹ የመረጃ ጦርነቱን በሚሰነዘረዉ ልክ መከላከል ካልተቻለ አሁን እየደረሰ ካለዉ ጉዳት የበለጠ ዋጋ ያስከፍላል ነው ያሉት፡፡

ምዕራባዊያን ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱት የሀሰት የመረጃ ተጽዕኖ በመንግሥታቸዉ የሚመራ እና የሚደገፍ መኾኑን መንግሥትም ይሁን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ተረድተው ችግሩን መቋቋም የሚችሉ የሚዲያ ተቋማትን መገንባት እና ተናቦ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ – ከአዲስ አበባ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ሠራተኞች እና ተማሪዎች ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ አድርገዋል፡፡
Next articleየወገኑ ሞት ልቡን ቢያስከፋው ፣ እንደ ጥራጊ ዘቅዝቆ ደፋው