
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ባካሄደው የሴኔት ስብሰባ ነው ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የክብር ዶክትሬት ለመስጠት የወሰነው፡፡
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ቅዳሜ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም በተማሪዎች ምረቃ ዕለት ተገኝቶ የክብር ዶክትሬቱን የሚቀበል ይሆናል በማለትም ዩኒቨርስቲው አስታውቋል፡፡
“ክብርህን ጠብቀህ ኢትዮጵያን ስላከበርክ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ይህን ክብር አበርክቶልሃል” በማለትም ይኒቨርስቲው ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ያለውን አድናቆት ገልጿል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
