
“ትህነግን በቆፈረችው ጉድጓድ እንቀብራለን፤ ኢትዮጵያን ከጠላት ፅዱ አድርገን የጀግኖች አባቶቻችን ታሪክ እንደግማለን” የዳባት ከተማ ውትድርና ሰልጣኝ ወጣቶች
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 06/2013 ዓ.ም (አብመድ) በርካታ የዳባት ከተማ ወጣቶች መንግሥት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ ተቀብለው ጠላትን በግንባር ለመዋጋት የውትድርና ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ከሰልጣኞቹ መካከል የዳባት ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ግዥ ባለሙያ የሆነው ሙሳ ይርጋ “የተሰጠንን ወታደራዊ ስልጠና ተጠቅመን፣ ሴት፣ ወንድ፣ ሳንል በተባበረ ክንዳችን ሊበላን ያሰፈሰፈውን ጠላት እስከመጨረሻው ለመዋጋት ዝግጁ ነን” ብሏል፡፡
የመንግሥት ክተት ጥሪ ከተላለፈበት ዕለት ጀምሮ የዳባት ከተማ ወጣት ወደ ጦር ግንባር ሄዶ አሸባሪውን ትህነግ ለመዋጋት በአንድ ልብ ተነስቷል ያለን ደግሞ በስልጠናው ያገኘነው የዳባት ከተማ የአማራ ወጣቶች ማኅበር ሥራ አስፈፃሚ ወጣት መካሻው አምባቸው ነው፡፡ ወጣት መካሻው “ትህነግ ጦርነት የከፈተው አማራን አጥፍቶ የኢትዮጵያን ታሪክ ሊያበላሽ፣ ሕዝቦቿን ሊያዋርድ፣ ለውጭ ወራሪ አሳልፎ ሊሰጣት ነው፡፡ ይሄን እኩይ ቡድን ከቆፈረው ጉድጓድ ቀብረን ኢትዮጵያን ከጠላት ጽዱ አድርገን የአባቶቻችንን ታሪክ ለመድገም ዝግጁ ነን” ብሏል፡፡
ሌላኛዋ የዳባት ከተማ ሴቶች ሕፃናትና ወጻቶች ጽሕፈት ቤት ባለሙያ የሆነችው ቢራራ መልኬ “እስካሁን ባለው የሕግ ማስከበር ከተማ ላይ ለሠራዊቱ ካደረኩት የቀለብ ዝግጅት በተጨማሪ በጦር ግንባር ሄጄ ከፊት ለመዋጋት ወስኜ ስልጠናውን እየወሰድኩ ነው” ብላለች፡፡
የዳባት ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ምክትል ኮማንደር ምህረት መለሠ እንዳሉት የዳባት ከተማ ወጣት ቀድሞውንም የውትድርና ስልጠና ጥያቄ ነበረው፡፡ ጥያቄው መልስ አግኝቶ ወጣቱ ስልጠናውን እየወሰደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ምክትል ኮማንደር ምህረት “ስልጠናው ከተደቀነብን የህልውና አደጋ ለመውጣት ጠላትን ለማጥቃትና አካባቢን በንቃት ለመጠበቅ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል” ነው ያሉት፡፡ ስልጠናውን ሁሉም ወጣት እየተሳተፈ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አድኖ ማርቆስ – ከዳባት
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m