አሸባሪው ትህነግ በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

323

አሸባሪው ትህነግ በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 21/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫው አሸባሪው ትህነግ አጎራባች ክልሎች ላይ ተከታታይነት ያለው ትንኮሳ እየፈጸመ መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ፕሬስ
ሴክሬታሪ ቢለኔ ስዩም አስታውቀዋል፡፡
ቢለኔ ስዩም በዛሬው ዕለት ለሀገር ውስጥ እና የውጭ ሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም አሸባሪው ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች በተከታታይነት ትንኮሳ እየፈጸመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ቡድኑ የግለሰቦችን ንብረት ማውደሙን እና መዝረፉንም ገልጸዋል፡፡
መንግሥት በትግራይ ክልል የተናጥል የተኩስ አቁም መድረሱን በመጥቀስም፥ ትህነግ ይህን የተኩስ አቁም በይፋ መጣሱንም
አውስተዋል፡፡
ይህም በተለይም ለችግር የተጋለጡ እና እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎችን ተደራሽ ለማድረግና ከአካባቢው ለማውጣት የሚደረገውን
ጥረት አስቸጋሪ አድርጎታልም ነው ያሉት፡፡
በተያያዘም ስድስት ኤርትራውያን ስደተኞች በአሸባሪው ትህነግ መገደላቸውንም ነው የገለጹት፡፡
ከዚህ ባለፈም ቡድኑ ህጻናትን ለውትድርና በመመልመል ንጹሃንን እንደ መሸሸጊያ እየተጠቀመባቸው መሆኑን በተጨባጭ
ማስረጃ ማረጋገጥ መቻሉንም አስረድተዋል፡፡
መላው ሕዝብም ይህን የአሸባሪውን ድርጊት በይፋ መቃወሙንም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
ፕሬስ ሴክሬታሪዋ መንግሥት የደረሰውን የተኩስ አቁም አክብሮ እየተንቀሳቀሰ ይገኛልም ብለዋል፡፡ ዘገባው የፋብኮ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአሸባሪው ትህነግ የሚያራምደው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሀገር የማፍረስ ተልዕኮውን ለማሳካት በመሆኑ መረጃን ከታማኝ ምንጮች መውሰድ እና ደጋግሞ ማጣራት እንደሚገባ የሥነ ተግባቦት ምሁር አስገነዘቡ፡፡
Next article“በሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳ የሚያዝም ሆነ የሚለቀቅ ቦታ የለም” የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ