
የአማራ ክልል መንግሥትን የክተት ጥሪ በመቀበል በባሕር ዳር ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተጀመረ።
በሰልፉም በአማራ ላይ የሚወራረድ አንድም ሒሳብ የለም፤ የእድገት ጉዞአችን በአሸባሪው ቡድን አይደናቀፍም፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚመኙ ሁሉ መጨረሻቸው ውድቀት ነው፤ ትህነግ ከኢትዮጵያ ማህጸን የበቀለ መርዛማ ተክል ስለሆነ ተባብረን እንክለው፤ የጁንታው ሀገር የማፍረስ ፍላጎት በኢትዮጵያ አሸናፊነት ይከሽፋል፤ ኢትዮጵያ በጀግኖች አፍራ አታውቅም፤ የምንዋጋው ለህልውናችንና ሀገር ለማዳን ነው፤ የውጭ ጣልቃ ገብነትን እንቃወማለን የሚሉ መልዕክቶች እየተስተጋቡ ነው።



