45 ዶክተሮች እና የህክምና ባለሙያዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ሙያዊ ድጋፍ ለመሰጠት ወደ ግንባር አቀኑ።

300
45 ዶክተሮች እና የህክምና ባለሙያዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ሙያዊ ድጋፍ ለመሰጠት ወደ ግንባር አቀኑ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 20/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ ሆስፒታሎች የተውጣጡ የህክምና ባለሙያዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊቱን ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡
የጤና ቢሮ ኃላፊው ዶክተር ዮሐንስ ጫላን ጨምሮ 45 ዶክተሮች እና የህክምና ባለሙያዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊቱን ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ዛሬ ሽኝት የተደረገላቸው።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀነአ ያደታ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ልዩ ልዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ለባለሙያዎቹ አሸኛኘት ተደርጓላቸዋል ።
የህክምና ባለሙያዎቹ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መድኃኒቶች እና የህክምና ቁሳቁስ ይዘው ተጉዘዋል።
ከዚህ ቀደም በሁለት ዙሮች ከከተማዋ የተለያዩ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች የተውጣጡ ዶክተሮች እና የህክምና ባለሙያዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ወደ ትግራይ ክልል መጓዛቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየዛሬ ውሎን የህልውና ዘመቻ አስመልክቶ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ የሰጡት አጭር መረጃ።
Next articleየአማራ ክልል መንግሥትን የክተት ጥሪ በመቀበል በባሕር ዳር ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተጀመረ።