አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለማጥፋት የክተት ጥሪውን ተቀብለው ለመዝመት መዘጋጀታቸውን የደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

268
አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለማጥፋት የክተት ጥሪውን ተቀብለው ለመዝመት መዘጋጀታቸውን የደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
 
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 20/2013 ዓ.ም (አሚኮ) “በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ለማዳን ወሎ ላይ የሚደረገው ትግል ወሳኝ ነው” የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሰሀ ወልደሰንበት
 
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 20/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ወሎ ዞን የዘመቻ ህልውና የክተት ጥሪ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል፡፡ በንቅናቄ መድረኩ ላይ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሰሀ ወልደሰንበትን ጨምሮ የፌዴራል የክልል እና የዞኑ የሥራ ኀላፊዎች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል፡፡
 
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰይድ መሀመድ “አሁን የምንገኝበት ወቅት ዓለምአቀፍ ድል የተቀዳጀንበት በሌላ በኩል ደግሞ የውስጥ እና የውጭ ጠላት ሀገራችንን ለመጠበቅ የተዘጋጀንበት ነው” ብለዋል፡፡ የሥራ ኀላፊዎች ራሳቸውን የማዘጋጀት፣ ኅብረተሰቡን የማደራጀት እና የማንቃት ሥራ መሥራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡
 
የደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪዎችም በአማራ ሕዝብ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ ለመመከት እንዲዘምቱ ጠይቀዋል፡፡
 
የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሰሀ ወልደሰንበት በአሁኑ ወቅት ማኅበረሰቡ አሁን የቀረበለትን የክተት ጥሪ ተቀብሎ እንዲዘምት ነው ያስገነዘቡት፡፡
 
የመድረኩ ተሳታፊዎችም አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለማጥፋት የክተት
ጥሪውን ተቀብለው ለመዝመት ቁርጠኛ መኾናቸውን ተናግረዋል፡፡
 
ዘጋቢ፡- ሀያት መኮነን – ከደሴ
 
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous article“በትግራይ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ላለው ችግር ሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስደው ሽብርተኛው የትህነግ ቡድን ብቻ ነው” ዶክተር አረጋዊ በርሄ
Next articleመንግሥት የአሸባሪውን ትህነግ ኋላ ቀር የጦር ስልት አካሄድ ለመቀልበስና የሀገርን ህልውና ለመታደግ ሁሉንም አማራጮች ሊወስድ እንደሚገባ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ገለጹ፡፡