“በትግራይ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ላለው ችግር ሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስደው ሽብርተኛው የትህነግ ቡድን ብቻ ነው” ዶክተር አረጋዊ በርሄ

193
“በትግራይ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ላለው ችግር ሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስደው ሽብርተኛው የትህነግ ቡድን ብቻ ነው” ዶክተር አረጋዊ በርሄ
 
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 20/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በትግራይ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ላለው ሰብዓዊ ችግር ሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስደው ሽብርተኛው የትህነግ ቡድን ብቻ መሆኑን የትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበርና የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ አስታወቁ።
 
ዶክተር አረጋዊ በተለይ እንዳስታወቁት፣ ጁንታው ቡድን እንኳን አሁን ሕዝቡ በዚህን ያህል ስቃይ ውስጥ ገብቶ ይቅርና ለውጡን አልቀበልም ብሎ ከኮበለለበት ጊዜ ጀምሮ እየተከሰቱ ለነበሩ ቀውሶችም ሆነ አሁን እየተፈጠረ ላለው እልቂት ሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስደው እርሱ ብቻ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።
 
ሽብርተኛው የጁንታው ቡድን የሕዝቡ መቸገር መራብ ምንም ጉዳዩ ባለመሆኑ እርዳታ የጫኑ 169 ከባድ መኪኖች አፋር ክልል ላይ እንዳይንቀሳቀሱ ጥቃት ከፍቷል፤ ይህ ተግባሩ የሚያሳየው ቡድኑ ለሕዝቡም ለሀገርም ጠንቅ መሆኑንና የራሱን ጥቅም ብቻ ፈላጊ ነው ብለዋል።
 
ሕዝቡ በጦርነትም ይሁን በረሃብ እየተሰቃየ ባለበት በዚህን ጊዜ የእርዳታ መግቢያ መስመርን መዝጋት ወይም ጥቃት ለመፈጸም መነሳት ከፍተኛ የሆነ ኢ- ሰብዓዊ ድርጊት ከመሆኑም በላይ አካባቢውን ሁሉ በሱ የጦርነት ነጋሪት ጉሰማ እንዲታመስ ሆን ብሎ ያቀደውና የፈለገው ነገር ነው ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ ይህ ደግሞ ሕዝቡም ሊገነዘበው ተቆርቋሪ ነን የሚሉ ሁሉ ሊያዩትና መፍትሔ ሊሰጡት የሚገባ እኩይ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። ዘገባው የኢፕድ ነው
 
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous article“አሸባሪው ትህነግ የማይካድራውን ጭፍጨፋ እና የ27 ዓመታቱን ጭቆና በየትኛውም ቦታ በማንም ሰው ላይ እንዲደግመው የሚፈቅድ አንድም አማራ የለም” የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች
Next articleአሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለማጥፋት የክተት ጥሪውን ተቀብለው ለመዝመት መዘጋጀታቸውን የደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡