
በባሕር ዳር ከተማ የሚኖሩ የቀድሞ የሠራዊት አባላት የተደረገውን የክተት ዘመቻ ለመቀላቀል አሸኛኘት ተደረገላቸው፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 20/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ቀደም ብሎ በተለያዩ ጊዜያት የሀገርን ዳር ድንበር ሲያስከብሩ ቆይተው እና ግዳጃቸውን አጠናቀው በመመለስ በባሕርዳር ከተማ በልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው የነበሩ የቀድሞ የመከላከያና ልዩ ኃይል አባላት የትህነግ አሸባሪ ቡድንን ለመመከት በክልሉ መንግሥት የተደረገውን የክተት ዘመቻ ተቀብለው መቀላቀላቸውን ተናግረዋል፡፡
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ በአሸኛኘቱ ተገኝተው እንደገለጹት በትግራይ ክልል አጎራባች የሚኖሩ የአማራዎች በትህነግ የግፍ አገዛዝ እንደባይተዋር ተቆጥረው ቦታቸውን፣ ልማታቸውንም፣ ሀብታቸውንና ማንነታቸውን ለዘመናት ተነጥቀው ቆይተዋል።
አሸባሪው ቡድን በተደረገው ፍትሕ የማስፈን ተግባር የተመለሰላቸውን የማንነት ጥያቄ ለመቀልበስና ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየታተረ ይገኛል ብለዋል፡፡
በመሆኑም ጀግናው መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ እያደረገ ያለው የሀገርን ክብር የማስጠበቅ ተጋድሎ በድል እንዲጠናቀቅ የሁላችንም አጋርነት አስፈላጊ በመሆኑ የክልሉ ምንግሥት የክተት ጥሪ ማስተላለፉን ገልጸዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም የባህርዳር ከተማ የቀድሞ ሠራዊት አባሎቻችን ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሰላም ማስከበር ግንባር ለመሄድ በመወሰናቸው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በማስረከብ በድን እንዲመለሱ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። መረጃው የባሕር ዳር ከተማ ኮምዩኒኬሽን ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m