
የሀገር መከላከያ ሠራዊቱን የሚቀላቀሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች እና የጤና ባለሙያዎች ሽኝት እየተደረገላቸው ነው።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 20/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ከአዲስ አበባ ከተማ መከላከያ ሠራዊቱን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች የሽኝት ሥነ ስርዓት በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ የሚገኘው የሽኝት ፕሮግራም ላይ የተለያዩ ፍከራዎች እና ኢትዮጵያዊ የሆነ ስሜትን የሚያንፀባርቁ ሙዚቃዎች እየቀረቡ ነው።
የሀገር ሽማግሌዎች ተጓዦቹን እየመረቁ ሲሆን “እናንተ የሰላም ተጓዦች ናችሁ፤ ኢትዮጵያን ዳግም አድዋ አድርጋችሁ ታስከብራላችሁ፤ በድል ተመለሱ” ብለዋቸዋል።
በሽኝት ሥነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ቀንአ ያደታ (ዶ.ር)፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡- አንዱአለም መናን-ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ