ለህዳሴ ግድቡ በ48 ሰዓታት ከዳያስፖራው 70 ሺህ ዶላር ተሰበሰበ።

214

ለህዳሴ ግድቡ በ48 ሰዓታት ከዳያስፖራው 70 ሺህ ዶላር ተሰበሰበ።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 19/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚደረግበት ድረ ገፅ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ከ583 ዳያስፓራዎች 70 ሺህ 380 ዶላር መሰብሰቡ ተገለፀ፡፡

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጰያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች www.mygerd.com የሚል ድረ ገጽ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ 70 ሺህ 380 ዶላር ድጋፍ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡

በተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እንደገለጹት ድረ ገፁ በተከፈተ 48 ሰዓታት ውስጥ 583 ለጋሾች ለህዳሴ ግድቡ 70 ሺህ 380 ዶላር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ድረ ገጹ የፈለጉትን መጠን ማስገባት እንዲችሉ ክፍት የሆነ ሲሆን 36 ሰዎች ግድቡን በተለያየ መንገድ እንደግፍ የሚል ዘመቻ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡

የተሰበሰበው በአማካኝ በሰዓት ሲታይ አንድ ሺህ 510 ዶላር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ ደግሞ ዲያስፖራው በቁጭት እየደገፈ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡ ዘገባው የኢፕድ ነው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“ማንኛውም የተቀመጠውን መመሪያን የሚጥስ የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር ለሚደርሰው አደጋ ኀላፊነት ይወስዳል” የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ
Next articleለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሃብት ለማሰባሰብና ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ለማሳየት ታላቅ የኢትዮጵያውያን ትዕይንት በዋሽንግተን ዲሲ ተካሄደ።