የመንግሥትን ጥሪ አልቀበልም በማለት በሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኀይሎች ላይ እርምጃ ተወሰደ።

437
የመንግሥትን ጥሪ አልቀበልም በማለት በሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኀይሎች ላይ እርምጃ ተወሰደ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 19/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ ግዳጁን በመፈፀም ላይ የሚገኘው የ2211ኛ ሻለቃ ሠራዊት አባላት የመንግሥትን ጥሪ አልቀበልም በማለት በሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኀይሎች ላይ እርምጃ ወሰደ፡፡
የ2211ኛ ሻለቃ ዋና አዛዥ ሻለቃ ዮሐንስ እውነቱ እንደተናገሩት ከሀገር ሰላም በተቃራኒ በመሆን ሕዝቡ በሰላም ወጥቶ በሰላም እንዳይገባ የጥፋትን ተልዕኮ እየፈፀሙ ባሉ ኀይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ 25 የሽፍታ አባላትን ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርኳቸዋል ፡፡
ጠላት ታጥቆ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ዘጠኝ ክላሽ መሳሪያ፣ ሶስት ኋላ ቀር መሳሪያ እንዲሁም በርካታ ቀስቶችን መማረካቸውንም አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም 185 የክላሽ ጥይት፣ 16 የብሬን ጥይትና አንድ የእጅ ቦምብ ይዘው በኅብረተሰቡ ላይ ጥቃት ለማድረስ ቢያስቡም ሠራዊቱ ቀድሞ በመንቃት ድል ማድረጉን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleʺለህልውና ዘመቻው ስኬት ቆርጠን እንነሳ” የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር
Next article“ማንኛውም የተቀመጠውን መመሪያን የሚጥስ የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር ለሚደርሰው አደጋ ኀላፊነት ይወስዳል” የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ