ʺለህልውና ዘመቻው ስኬት ቆርጠን እንነሳ” የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር

153
ʺለህልውና ዘመቻው ስኬት ቆርጠን እንነሳ” የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር
ባሕር ዳር: ሐምሌ 19/2013 ዓ.ም(አሚኮ) የሰሜን ወሎ ዞን ሕዝብ የክተት ጥሪውን ተቀብሎ ለትግል መንቀሳቀሱን አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
የዞኑ አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን በማኅበራዊ ትስሰር ገፁ ባወጣው መልእክት ትግላችን ላንጨርስ አልጀመርነውም፤ ትግሉ የሀገርን ሉዓላዊነት የማስቀጠል የሞት ሸረት ጉዳይ ነው ብሏል፡፡ ይህ ወቅት በአንድነት ዘብ ቁመን ታሪካዊ አሻራችንን የምናሳርፍበት፣ ደማቅ ታሪክ የምንፅፍበት ነው ሲሉም ገልጿል፡፡
የትህነግ አሸባሪ ቡድን ሀገርን የማፍረስ ተልዕኮ አንግቦ የሚንቀሳቀሰው የተራዘመ የትግል ስልትን እየተጠቀመ የመጣ ነው ያለው አስተዳደሩ አሁን ላይ ግን በግልጽ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን በሚል አቋሙን እንደሚያራምድ ገሀድ ወጥቷል ነው ያለው፡፡
ኢትዮጵያ በየዘመናቱ ከውስጥም ከውጭም ሊያጠፋትና ክብሯን ዝቅ ሊያደርጉ የመጡ ኃይሎችን ሁሉ አሳፍራ የመለሰች የጥቁር አፍሪካ የነፃነት ምልክት መሆኗንም ገልጿል፡፡
የትህነግ አሻባሪ ቡድን ከውጭ ጠላቶቻችን ባልተናነሰ ሀገርን የማፍረስ ተልዕኮ አንግቦ ርብርብ እያደረገ ይገኛል ብሏል፡፡
በአንፃሩ ለሀገራቸው ሉዓላዊነትና ክብር ሲሉ መስዋእት የሆኑ፣ ለትውልድ የሚሸጋገር አኩሪ ገድል የፈፀሙ፣ ሀገረ መንግሥትን ያነፁ በዕንቁ ልጆቿ ታፍራና ተከብራ የምትኖር ሀገረ ኢትዮጵያ የመሠረቱ የትየለሌ ናቸውም ነው ያለው፡፡
ሀገር የገጠማትን ፈተና በሕዝባዊ ትግል መመከት የወቅቱ ቁልፍ ጉዳይ ነው፤ ለዘህ ደግሞ የክልሉ መንግሥት የክተት ጥሪ አውጇል፤ አዋጁ የሀገርን ህልውና የማስጠበቅና ሀገረ መንግሥትን የማፅናት የክተት ጥሪ ነውም ብሏል፡፡ ይህ ጥሪ ታሪካዊ ጥሪ ነው፤ ይህ ጥሪ የህልውና ጥሪ ነው፤ ይህ ጥሪ ለነጻነትና ለሉዓላዊነት የሚከፈል ሀገርን የመታደግ የህልውና ጥሪ ነው። ይህ አዋጅ ሕብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ የመገንባት የሚደረግ የህልውና ዘመቻ ነው ሲልም አስታውቋል።
በዞኑ በመንግሥት የተላለፈውን የክተት ጥሪ ተከትሎ የተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተግብቷል ያለው አስተዳደሩ ከዞን እስከ ወረዳ ለልዩ ኃይልና ለመከላከያ ሠራዊት የሚመዘገበው ወጣት እየተመመ ነውም ብሏል፡፡
የቀድሞ የሠራዊትና የልዩ ኃይል ምልስ
ወታደሮች ወደ ግንባር እየተሰለፉ የዘመቻው አካል ሆነዋልም ነው ያለው፡፡ ለሕዝባዊ ሠራዊቱ የሚደረግ የሞራል፣ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏልም ነው የተባለው፡፡
በዞኑ የሚገኙ ማንኛውም የመንግሥትን መሳሪያ የታጠቀ፣ የግል መሳሪያ የታጠቀ፣ ለግዳጅ ብቁ የሆነ ወጣት ሁሉ የክተት ጥሪውን ተቀብሎ ለህልውና ዘመቻ የተላለፈውን ጥሪ አክብሮ በዘመቻው ለመሳተፍ የተግባር ስምሪት ውስጥ ገብቷል ብሏል፡፡
በጦር ግንባር ድል ያልቀናቸው የትህነግ ጁንታ ቡድን ለሚያሰራጩት አሉባልታ ወሬ ጆሮ መስጠት አያስፈልግም ያለው የዞን አስተዳደሩ ከእውነተኛ መረጃ ይልቅ የትህነግ የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት ሐሰተኛ መረጃዎች በስፋት እያሰራጩ በመሆኑ ለዚህ ሐሰተኛ መረጃና አሉባልታ ወሬ ጆሮ ባለመስጠት ሁሉም የኅብረሰብ ክፍል የተጋረጠውን የህልውና አደጋ በጋራ መመከት ወቅቱ የሚጠይቀው ታሪካዊ ኃላፊነት ነው ሲል አስታውቋል።
የሰሜን ወሎ ሕዝብ ዘመቻ ለህልውና የክተት ጥሪ ተቀብሎ ዛሬም እንደትናንቱ የአባቶቹን ገድል ሊተግበር ከጫፍ እስከ ጫፍ ተንቀሳቅሷልም ብሏል፡፡
እንደ ሀገር ኾነ እንደ አማራ የተደቀነብን የህልውና ዘመቻ በድል አጠናቀን ወደ ልማት የምንመለስበት ጊዜ ቅርብ ነው ብሏል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleአሸባሪዉ ትህነግ በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተዉ ጦርነት በሀገር ላይ የተቃጣ ጥቃት በመኾኑ ይህን ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መኾኑን የኦሮሚያ ተመላሽ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ማኅበር ገለጸ፡፡
Next articleየመንግሥትን ጥሪ አልቀበልም በማለት በሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኀይሎች ላይ እርምጃ ተወሰደ።