በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት የክልሉ መንግሥት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ በመቀበል አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ።

209

በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት የክልሉ መንግሥት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ በመቀበል አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውና ተስፋፊው የትህነግ ጁንታ በአማራ ሕዘብ ላይ የጀመረውን ጦርነት ለመቀልበስና ቡድኑን ለመደምሰስ በአማራ ክልል መንግሥት የተጠራውን የክተት ጥሪ በመቀበል ለህልውና ዘመቻው ዝግጁ መሆናቸውን በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ የሚኖሩ የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ገለጹ።

የቀድሞ ሠራዊት አባላቱ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ዉይይት በኮምቦልቻ ከተማ እያካሄዱ ሲሆን በውይይታቸው
“ምንም እንኳ እድሜያችን ቢገፋም ሀገራችን ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር ለመመከት መንግሥት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ እድሜአችን 18 ነው” ብለዋል።

“የትህነግን ተንኮልና ለአማራ ያለውን ጥላቻ ድሮም እናውቀዋለን፤ እንኳን በጦርነት ድሮም በመዋሸት የታወቀ የሀገር ጠላት ስለሆነ ማኅበረሰቡ በውሸት መረጃ መሸበር የለበትም” ነው ያሉት።

በመድረኩ የተገኙት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አህመድ የሱፍ (ኢንጅነር) የቀድሞ ሠራዊት አባላት የአከባቢ ሰላምን ከማስጠበቅ ጀምሮ በማማከርና በሌሎች በሚጠበቅባቸው ሥራዎች ከከተማ አስተዳደሩ ጎን እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

ዘጋቢ:–ከድር አሊ–ከኮምቦልቻ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleʺጠብ አጫሪነት ያባት አይደለም፤ የመጣበትን ጠላት መክቶ መጣል ግን የአባት ነው” የወልድያ ከተማ አስተዳደር
Next articleበባሕር ዳር የቆየው የኤርትራ ብሔራዊ የእግርኳስ ቡድን በአማራ ክልል መንግሥት ሽኝት እየተደረገለት ነው።