
ʺጠብ አጫሪነት ያባት አይደለም፤ የመጣበትን ጠላት መክቶ መጣል ግን የአባት ነው” የወልድያ ከተማ አስተዳደር
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የወልድያ ከተማ ወጣቶች የአሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ እየተደረገ ባለው ሂደት ደጅንነታቸውና ጀግንነታቸውን እያስመሰከሩ ነው፡፡
የወልድያ ከተማ አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልእክት ጁንታዎቹ ቦታዎችን የሚቆጣጠሩት በፌስቡክ ብቻ ነው ብሏል፡፡
ʺጠብ አጫሪነት ያባት አይደለም፤ የመጣበትን ጠላት መክቶ መጣል ግን የአባት ነው” ብሏል አስተዳድሩ። የወልድያና አካባቢዋ ወጣት ከጸጥታ ኃይሉ ጎን ተሰልፎ ስንቅ በማቀበልና አካባቢውን በመፈተሽ ከአለኝታው ከጸጥታ ኃይሉ ጋር እና ከራያ ቆቦ ወገኑ ጎን ግንባር ተሰልፏልም ብሏል።
ጠላት መውጫ ቀዳዳ ጠፍቶት በቆፈረው ጉድጓድ እራሱ እየገባ፤ በጫረው ክብሪት እራሱ እየተቃጠለ ነውም ተብሏል። “ከሺህ ጦረኛ አንድ ወሬኛ” በሚለው አባባል የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ማሽኑም ከሽፏል ብሏል አስተዳደሩ።
የከተማዋ ነዋሪም አሁንም አልፎ አልፎ የሚረጩ የፕሮፓጋንዳ መርዞችን በየዋህነት የሚቀበሉ ጆሮዎችን በማጽዳት የመጨረሻው የድል ፍጻሜ እስኪደረስ በየፈርጁ የተሰጠውን ተግባር አጠናክሮ እንዲወጣም አሳስቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m