የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ክልል መንግሥትን የክተት ጥሪን እንደሚቀበል አስታወቀ።

414

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ክልል መንግሥትን የክተት ጥሪን እንደሚቀበል አስታወቀ።

ፓርቲው ለአማራና ለኢትዮጵያ ሕዝቦችም መልዕክት አስተላልፏል፣ ቀጥሎ ቀርቧል።

ለተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች የድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎች፤

ድርጅታችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገር ሉዓላዊነትና አንድነትን ለማስጠበቅ፣ ህግና ስርዓትን ለማስፈንና ሀገርን ለማዳን የጀመረውን ጥረትና የክልል መንግስታት እያደረጉት ያለውን ቁርጠኝነት የተሞላበት የተባበረ እንቅስቃሴ ንቅናቄያችን በአክብሮት ይመለከተዋል።

ዘግይቶም ቢሆን የአማራ ክልል መንግሥት ከፍተኛ የሆነ የህልውና ስጋት የተጋረጠበትን አገረ መንግስትና በጠላትነት የተፈረጀውን ህዝባችን ለመታደግ የአወጀውን የክተት ጥሪ በሙሉ ልብ የምንቀበለውና ለተግባራዊነቱም የበኩላችን ከፍተኛ ጥረት የምናደርግ መሆኑን እየገለፅን የክልሉ መንግስትም አልፎ አልፎ የሚታዩ አስተዳደራዊ ችግሮችን በመፍታት የመሪነት ሚናውን በተገቢው መንገድ እንዲወጣ እንጠይቃለን ።

መላው የድርጅታችን አመራሮች አባላት ደጋፊዎቻችንና ህዝባችን ይህን ጥሪ በመቀበል በየደረጃው ካለው መንግስታዊ መዋቅር ጋር በመቀናጀት የክተት ዘመቻውን እንድትቀላቀሉ እናሳስባለን ።

እሁድ ሐምሌ 18/ 2013

Previous articleሁሉም አማራ ወደ ግንባር እንዲሰለፍ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጥሪ አቀረቡ።
Next articleʺጠብ አጫሪነት ያባት አይደለም፤ የመጣበትን ጠላት መክቶ መጣል ግን የአባት ነው” የወልድያ ከተማ አስተዳደር