
“ኢትዮጵያን በታሪካዊ ዉኃ ልኳ ለማስቀመጥ እና ለትዉልድ ለማስረከብ ዛሬም እንደ ትናንቱ እንዋደቃለን” የኢትዮጵያ ሠራዊት የድጋፍ እና የልማት ማኅበር
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሀገሩ እየተዋደቀ ባለበት በዚህ ወቅት ሁለንተናዊ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸዉን የኢትዮጵያ ሠራዊት የድጋፍ እና የልማት ማኅበር አባላት ገለጹ፡፡ የማኅበሩ አባላት የድጋፍ ድምጻቸዉን በአዲስ አበባ መስቀል አደበባይ አሰምተዋል፡፡
የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት የድጋፍ እና የልማት ማኅበር አባላት የመከላከያ ሠራዊት ሀገርን ከጥቃት ለመታደግ እየከፈለ ያለዉን የህይዎት መስዋእትነት ለመደገፍ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የድጋፍ ድምጻቸዉን አሰምተዋል፡፡
አሸባሪዉ ትህነግ ኢትዮጵያን ለውጭ ኀይሎች አሳልፎ ለመስጠት እየሠራ እንደሆነ የማኅበሩ ሰብሳቢ ሃምሳ አለቃ ብርሃኑ ዓማረ ገልጸዋል፡፡ “መከላከያ ሠራዊቱ ይሄን እኩይ ተግባር እየተፋለ ባለበት ወቅት የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት የድጋፍ እና የልማት ማኅበር አባላት እጃችንን አጣጥፈን የምንቀመጥበት ወኔ የለንም፤ አባቶቻችን ደማቸዉን አፍሰዉ የገነቧትን ኢትዮጵያ እኛም ዋጋ ከፍለን በታሪካዊ ዉኃ ልኳ ለማስቀመጥ እና ለትዉልድ ለማስረከብ ዛሬም እንደ ትናንቱ እንዋደቃለን” ብለዋል፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ የኢትዮጵያ ጠላቶች ዉድቀታችንን ለማፋጠን የሚጠቀሙት ቁልፍ መንገድ አንድነታችንን መናድ ነዉ እና ይህን በመረዳት አንድ ሆነን ችግሩን ልንሻገር ይገባል ብለዋል፡፡ እንደ ኮሎኔሉ ማብራሪያ በጀግንነት የሚታወቀዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት አሁን ላይ ፈተና የሆነበት የትህነግ ቡድን ሳይሆን ከጀርባ ሆኖ ለጦርነት የሚያሰልፋቸዉን ህጻናትን፣ አዛዉንቶችንና እና ነፍሰ ጡር እናቶችን ገደልኩ እና ማረኩ ለማለት ግራ መጋባቱ ነዉ፡፡
በመሆኑም ወታደራዊ ጥበብ ተጠቅመን ከሀዲዉን እና አሸባሪዉን ቡድን ላይመለስ እንሸኘዋለን ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡-በለጠ ታረቀኝ -ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m