
“ለሀገራችን ሉዓላዊነት ዛሬም እንቆማለን” የሰሜን ሸዋ ዞን የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡
“ለሀገራችን ሉዓላዊነት ዛሬም እንቆማለን” የሚል እና መሰል መልዕክቶችን አንግበው ነው ሰልፍ የወጡት፡፡
ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ባለው የድጋፍ ሰልፍ ለሀገር ህልውና ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው ትህነግ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀመዉ ታላቅ ክህደትና በንጹሃን ላይ ያደረገው የዘር ጭፍጨፋ ይቅር የማይባል መሆኑን ነው ሰልፈኞቹ የገለጹት።
ለሀገር አፍራሹ ቡድን በመወገን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ እያሳደሩ ያለውን ጫና በጋራ መከላከል እንደሚገባም የቀድሞ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡- ዮሐንስ ንጉስ-ደብረ ብርሃን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m