“አሸባሪው ትህነግ የኢትዮጵያ ሕዝብን በማጋጨት ዕድሜውን ለማራዘም ጥረት የሚያደርግ ስብስብ ነው” የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ

142
“አሸባሪው ትህነግ የኢትዮጵያ ሕዝብን በማጋጨት ዕድሜውን ለማራዘም ጥረት የሚያደርግ ስብስብ ነው” የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአሸባሪው ትህነግ ስብስብ የመንግሥትን ተናጠላዊ የተኩስ አቁም ውሳኔን ያልተቀበለ፣ በተፈጥሮው ሰላም የማይፈልግና የኢትዮጵያ ሕዝብን በማጋጨት ዕድሜውን ለማራዘም ጥረት የሚያደርግ ቡድን መሆኑን የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ገለጹ።
የአዳማ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ሰልፍ አድርገዋል።
አቶ ጌታቸው በአዳማ ከተማ የተካሄደውን የሕዝቡን የድጋፍ ሰልፍ አስመልክተው ትናንት እንደገለፁት፤ የአሸባሪው ጁንታ ትህነግ ስብስብ በተፈጥሮው ሰላም የማይፈልግና የኢትዮጵያ ሕዝብን በማጋጨት ዕድሜውን ለማራዘም ጥረት የሚያደርግ ነው።
አሸባሪውን ቡድን ለመመከት የኦሮሞ ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር ለመከላከያው ድጋፍ ማድረግ አለብን በማለት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ነው ብለዋል። አሸባሪው ጁንታ እየፈፀመ ያለው ሀገር የማፍረስ ድርጊት በመሆኑ የኦሮሞ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ለመከላከያው ድጋፉን ይቀጥላል ነው ያሉት። ኢፕድ እንደዘገበው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleʺየአማራ ሕዝብ ከተዘናጋ ለመጥፋት መርጧል ማለት ነው” በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የሕግ መምህር
Next articleየአማራ ሕዝብ ልዩ ኀይሉን ለማጠናከርና ደጀን ለመኾን እያደረገ ያለውን ተነሳሽነት ለማበረታታት የአማራ ፖሊስ የማርች ባንድ አባላት በጎንደር ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ትርዒት እያሳዩ ነው።