ʺአሸባሪውን የትህነግ ቡድን ከምድረ ገፅ ማጥፋት አለብን” ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ

918

ʺአሸባሪውን የትህነግ ቡድን ከምድረ ገፅ ማጥፋት አለብን” ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ልዩ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም የአሸባሪው ትህነግ ተቀዳሚ ዓላማ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው ብለዋል።
አሸባሪው ትህነግ በአማራና አፋር ክልል ጦርነት በመጀመር ሌላውን ኢትዮጵያዊ ሊያጠቃ ትንኮሳ እየፈጸመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ የአሸባሪው ቡድን ኢትዮጵያን የማፍረስ እኩይ ሴራ በመረዳት በህልውና ዘመቻው ላይ እንደሚገኝ
አመላክተዋል። አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ከምድረ ገፅ ማጥፋት አለብን ነው ያሉት፡፡
የአሸባሪ ቡድኑን የሐሰት ፕሮፓጋንዳና አሉባልታ የሚያናፍሱ በሕዝብ ውስጥ ያሉ ተላላኪዎችን ማኅበረሰቡ በንቃት ሊከታተል
ይገባል ብለዋል ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ።
መንግሥት ያስተላለፈውን ጥሪ ተቀብሎ ሕዝቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል። ትግሉን ወጣቱ በጉልበቱ፣ ሕዝቡና ባለሃብቱ
በሎጅስቲክ ሊያግዙ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ነው የጠየቁት፡፡
የጦር ልምድ ያላቸው መሪዎችና ተዋጊዎች ወደ ልዩ ኃይል እየተቀላቀሉ መሆኑንም አስታውቀዋል።
የትግራይ ሕዝብ ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል ያሉት ብርጋዴር ጄኔራሉ ዛሬ እየሆነ ያለው ጊዜያዊ ነው፤ ዘላቂ ወንድሙ ግን
የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ብለዋል።
አሸባሪው ትህነግ ሕጻናትን ወደ እሳት እየማገደ መሆኑን የገለጹት አዛዡ የትግራይ ሕዝብ ልጆቹን ከዚህ ውድመት ማዳን
እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የአማራ ልዩ ኃይል ከሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ጋር እየተናበበ በቅንጅት እየተዋጋ ስለመሆኑም አስታውቀዋል።
ለኢትዮጵያ ዘብ ቆመው አሸባሪውን ቡድን በግንባር በመፋለም ላይ ላሉ የጸጥታ ኃይሎች ምስጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡- ካሳሁን ኃይለሚካኤል
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“ሕዝብ በሰላም ወጥቶ በሰላም ይገባ ዘንድ ሠራዊታችን በዱር በገደሉ ለሚያደርገው ተጋድሎ ደም መለገስ ለነገ የማይባል ተግባር ነው” የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች
Next article“የሕዳሴው ግድብ የውኃ ሙሌት ግብጽና ሱዳን ሲያሰራጩት የነበረውን ሐሰተኛ መረጃ ያጋለጠ ነው” የዓረብ ሀገራት ግንኙነት ተመራማሪ ዛይድ ዜዳን አል-ሀሪሪ