
የሲዳማ ክልል ሁለተኛ ዙር የልዩ ኃይል አባላትን ለሀገራዊ ጥሪ ሊልክ ተዘጋጅቷል፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 17/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሲዳማ ክልል ሁለተኛ ዙር የልዩ ኃይል አባላትን ለሀገራዊ ጥሪ ለመላክ መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
ልዩ ኃይሉ የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ እየሠራ መሆኑንና ሀገራዊ ጥሪን በመቀበለም ለሀገር እድገት ነቀርሳ የሆነውን አሸባሪው የሕወሓት አጥፊ ቡድን ለማስወገድ ቆርጠው ተነስተዋል ነው ያለው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፡፡
አሸባሪው ሕወሓት በፊትም ለሕዝብ መለወጥና አንድነት ደንታ የሌለዉ ቡድን በመሆኑ የሕዝቦችን አንድነት ለማረጋገጥና ቡድኑን እንዲወገድ ልዩ ኃይሉ የሚተጋ መሆኑን ነዉ ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና የገጽታ ግንባታ ዳሬክተር ኮማንደር መስፍን ዴቢሳ እንደገለጹት ልዩ ኃይሉ ሀገራዊ ጥሪውን በመቀበል በወኔ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡
ጥሪዉን በማክበር ለሀገሪቷ አንድነት የሚሠሩት የልዩ ኃይል አባላቱ ዛሬ በሀዋሳ ሽኝት እንደሚደረግላቸውም ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ መግለጻቸውን ፋብኮ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ