
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚያደርጉበት ድረ ገጽ አዘጋጀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኢትዮጵያውያን በበይነ መረብ ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚያደርጉበት ድረ ገጽ ይፋ አድርጓል፡፡ ድረ ገጹ www.mygerd.com የተሰኘ ነው፡፡
በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የኢትዮጵያ የብልጽግና ራእይ እውን እንዲሆን፣ ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ አስተዋፅዖአቸውን በቀላሉ ማበርከት የሚችሉበት መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ