“ሕዝባዊ ደጀንነታችን አሁንም ተጠናክሮ ይቀጥላል” የሰሜን ወሎ ዞን

109
“ሕዝባዊ ደጀንነታችን አሁንም ተጠናክሮ ይቀጥላል” የሰሜን ወሎ ዞን
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ወሎ ዞን ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ መረጃ አጋርቷል፡፡
በራያ ግንባር ጀግናው ሕዝባዊ ሠራዊታችን በከፍተኛ ጀብዱ ድል እያስመዘገበ ይገኛል፤ ይህ ጦርነት የሀገር ኩራት፣ ዋልታና ማገር የሆነው የመከላከያ ሠራዊታችን ግዳጅ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ሀገራዊ ተልዕኮ ነው ብሏል፡፡
ሠራዊቱ ሕዝባዊ መሠረት ያለው በመሆኑ የሕዝቡን ድጋፍና እንክብካቤም ይሻል፤ ሕዝቡ ለሠራዊቱ የሚያደርገውን ሕዝባዊ ደጀንነት በማስቀጠል የሞራል፣ የቁሳቁስና የስንቅ ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያለው፡፡
የሕወሓት ጁንታ ቡድን የፈጠራ ወሬ ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን ቀድሞም የነበረ አሁንም የቀጠለ ነው፤ የሕዝቡን ሥነ ልቦና ለመሸርሸር የማይጠቀሙት የአጀንዳ ዓይነት የለም፡፡ ለዚህ ደግሞ በሰው ኃይልና በሎጅስቲክ የሚመራ የተደራጀ የሳይበር ሠራዊት እንዳላቸው ግንዛቤ መውሰድ እንደሚገባ ገልጿል፡፡
ሕዝቡ በሐሰተኛ ወሬ ሳይደናገር ለሕዝባዊ ሠራዊቱ ደጀን ኾኖ ዘብ ከመቆም በተጨማሪም አጋርነቱን በተግባር ሊያረጋግጥ እንደሚገባም አስታውቋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየሀረሪ ክልል የካቢኔ አባላት ለሁለተኛ ጊዜ የአንድ ወር ሙሉ ደምወዛቸውን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለገሱ።
Next articleየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚያደርጉበት ድረ ገጽ አዘጋጀ፡፡