
የሀረሪ ክልል የካቢኔ አባላት ለሁለተኛ ጊዜ የአንድ ወር ሙሉ ደምወዛቸውን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለገሱ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የክልሉ መሥተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) አባላት ዛሬ ባካሄዱት ስብሰባ ነው አባላቱ ለሁለተኛ ጊዜ የአንድ ወር ደምወዛቸውን ለመስጠት የወሰኑት።
የካቢኔ አባላቱ ከወራት በፊትም የወር ደምወዛቸውን መለገሳቸው ይታወሳል፡፡
የመሥተዳድር ምክር ቤት አባላቱ በቀጣይም ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን ከሀረሪ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ትስስር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ