
ተጨማሪ የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ወደ ግዳጅ ቀጠና ሊያመሩ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ሀገር ላይ የጋረጠውን አደጋ ለመቀልበስ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት እየሠሩ ይገኛሉ።
የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ሀገራዊ ጥሪውን በመቀበልም ከጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ጎን መቆሙን ትግሉን በመቀላቀል አረጋግጧል።
ዛሬ ተጨማሪ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላትም ወደ ግዳጅ ቀጠና እንደሚያመሩ ከደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m