በደቡብ አፍሪካ አመጽ የሞተ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

162
በደቡብ አፍሪካ አመጽ የሞተ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸውን የሥራ ክንውን አስመልከቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም በደቡብ አፍሪካ በተከሰተው አመጽ 117 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፤ በርካቶችም ቆስለዋል ንብረት ወድሟል ነው ያሉት። ከነዚህ መካከል የሞቱ ኢትዮጵያዊያን የሉም ያሉት አምባሳደር ዲና የቆሰሉ ግን መኖራቸውን የኢትዮጵያ ኢምባሲ በመረጃ ማረጋገጡን ጠቁመዋል።
የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውኃ ሙሌትን በተመለከተ ለግብጽና ሱዳን ቀደም ብሎ መረጃ የተላከላቸው መሆኑን ያነሱት ቃል ዐቀባዩ ሙሌቱ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን በጎርፍ ከመጥለቅለቅ ያድናል በሚል በኢትዮጵያ በኩል ሲነሳ የነበረው ሐሳብ ትክክል መሆኑን በዚህ የክረምት ሙሌት ማረጋገጥ እንደተቻለም ቃል ዐቀባዩ ተናግረዋል።
የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ ተከትሎ የተለያዩ አካላት ውሳኔውን በበጎ መልኩ አለመቀበላቸው ኢትዮጵያውያንን ያስቆጣ ነው፤ እየተቃወሙትም ይገኛሉ ነው ያሉት።
ለትግራይ የሰብዓዊ ርዳታ ድጋፍ በተጠየቀው መልኩ አሁን ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ መቀሌ እየተጓጓዘ እንደሚገኝም ነው ያብራሩት።
ከሳዑዲ አረቢያ ዜጎችን የመመለስ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡
በኢትዮጵያ ላይ ያለው ጫና እየተቀየረ መምጣቱንም አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡-አንዱዓለም መናን- ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየ2013 የበጀት ዓመት የክንውን ግምገማ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
Next articleለአሸባሪው ሕወሓት ቡድን በተለያየ መንገድ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ 28 ግለሰቦችና ንብረቶቻቸው በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡