ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሽብርተኛውን ትህነግ ለመደምሰስ በሚደረገው ዘመቻ ሁለንተናዊ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ሴቶች ማኅበር ጥሪ አቀረበ፡፡

131

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሽብርተኛውን ትህነግ ለመደምሰስ በሚደረገው ዘመቻ ሁለንተናዊ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ሴቶች ማኅበር ጥሪ አቀረበ፡፡

ባሕር ዳር: ሐምሌ 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ሽብርተኛውን ትህነግ የሚያወግዝ እና የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የአዲስ አበባ ሴቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ሁሉሀገርሽ ታዘዘ ሽብርተኛው ትህነግ ባለፉት ዓመታት የተዘረጉለትን የሰላም አማራጮች ባለመቀበል ሀገር ለማተራመስ እኩይ ድርጊት መፈጸሙን ጠቅሰዋል፡፡ ዛሬም የትግራይን ሕዝብ ዋነኛው የሰቆቃው ገፈት ቀማሽ በማድረግ ለተጨማሪ ስቃይ እየዳረገ ነው ብለዋል፡፡

በሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ለትግራይ ሕዝብ አንዳች የሚረባ ነገር ያልሠራው ሽብርተኛው ትህነግ ዛሬም በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሕዝቡን ከሌላው ሕዝብ ጋር ለማጋጨት እና ደም ለማፋሰስ እየሠራ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀገርን ለማፍረስ እየሠራ ያለውን ሽብርተኛውን ትህነግ ለመደምሰስ በሚደረገው ዘመቻ ሁለንተናዊ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ፕሬዝዳንቷ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሽብርተኛው ትህነግ የትግራይ ብሎም የሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ጠላት መሆኑን ነው ፕሬዝዳንቷ የገለጹት፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ከጀርባ በመውጋት የፈጸመው ክህደት ሌላኛው ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ዛሬም ሽብርተኛ ቡድኑ እየፈጸመ ያለውን ጥፋት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቃ ማለቱን ነው ወይዘሮ ሁሉሀገርሽ የገለጹት፡፡ ከዚህ ሽብርተኛ ቡድን የጥፋት ተልዕኮ
ሀገርን እና ሕዝብን ለማዳን በሚደረገው ዘመቻ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

ዘጋቢ:- ትርንጎ ይፍሩ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleውጊያ ለመክፈት ተደጋጋሚ ሙከራ ያደረገው የአሸባሪው ትህነግ ቡድን ሰብዓዊ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑን የምኒልክ ብርጌድ አስታወቀ።
Next article“የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር የታላቁ የኢትጵያ ህዳሴ ግድብን ከደለል ለመጠበቅ የሚያግዝ በመሆኑ ሁሉም በንቃት መሳተፍ ይገባዋል” የአማራ ክልል ምክትል ርእስ መሥተዳደር ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ.ር)