“የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለተፋሰሱ ሀገራት እውነተኛ የትብብር ማዕከል ሆኖ ይቀጥላል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

143

“የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለተፋሰሱ ሀገራት እውነተኛ የትብብር ማዕከል ሆኖ ይቀጥላል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

ባሕር ዳር: ሐምሌ 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በስኬት የተጠናቀቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት ለዓባይ ወንዝ የታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ጭምር የትብብር ማዕከል ሆኖ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው በአረብኛ ቋንቋ ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያ ቀድም ብላ ባስቀመጠችው እቅድ መሰረት በሐምሌ መግቢያ ወር ላይ ሁለተኛውን የህዳሴው ግድብ ሙሌት ያለምንም እንከን ማከናወኗን አመልክተዋል፡፡

የክረምቱን ዝናብ ተከትሎ በተከናወነው ሙሌት የታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ላይ ተፅዕኖ በማይፈጥር መልኩ በጥንቃቄ መከናወኑን ተናግረዋል። ይህም ከፍተኛ መጠን ያለውን ጎርፍ መቆጣጠር በሚያስችል መልኩ መፈፀሙን እንዲገነዘቡ በመልዕክታቸው ጠይቀዋል፡፡

ሁለተኛው ዙር የህዳሴው ግድብ የውኃ ሙሌት ወዲፊትም ቢሆን በአንዳቸውም የታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ላይ ጉዳት እንደማያስከትል ጭምር በመገንዘብ፣ ይልቁንም ግድቡ በተፋሰስ ሀገራት መካከል የእውነተኛ ትብብር ምንጭ ሆኖ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“ሠራዊታችን ብሔራዊ አርማችን ነው፤ የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው” የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Next articleውጊያ ለመክፈት ተደጋጋሚ ሙከራ ያደረገው የአሸባሪው ትህነግ ቡድን ሰብዓዊ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑን የምኒልክ ብርጌድ አስታወቀ።