አሸባሪው የትህነግ ቡድን የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ ተጋለጠ።

300
አሸባሪው የትህነግ ቡድን የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ ተጋለጠ።
ባሕር ዳር: ሐምሌ 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትህነግ ቡድን የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ መጋለጡን የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
የሽብር ቡድኑ በዕቅዱ መሠረት ከትግራይ ክልልና ከሱዳን በሚያስገባቸው ሠርጎ ገቦች አማካኝነት ጭፍጨፋውን ለመፈጸም ማቀዱን ያሳያል።
የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ እንደገለጸው ይሄንን ለማድረግ እንዲመች በራያና አፋር በኩል ተደጋጋሚ ትንኮሳ በመፈጸም የመከላከያ ሠራዊቱንና የአማራ ልዩ ኃይልን ትኩረት ለማዛባት ሞክሯል።
የጦር ኃይሉን ወደ ራያና አፋር ሲሰባሰብና የምዕራቡ ኃይል ሲሳሳ በዚያ በኩል ጥቃት በመክፈት ድርጊቱን ለመፈጸም ማቀዱን ያሳያል ብሏል መረጃ ማጣሪያው።
ጁንታው ከሰሞኑ የአማራ ልዩ ኃይልና መከላከያ በሑመራ ጭፍጨፋ እንደሚፈጽሙ በማኅበራዊ ሚዲያ ማሠራጨት እንደሚጀምር ዕቅዱ ያሳያል ሲል የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአሸባሪውን ትህነግ ሀገር የማፍረስ ተልዕኮን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
Next articleቺርቤዋ አምሊ 15 ጌርክ 2013 ም.አ(አሚኮ)