
የአሸባሪውን ትህነግ ሀገር የማፍረስ ተልዕኮን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ በጥዋቱ የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፍ አሸባሪውን ትህነግ የሚቃወም፣ ሀገር የማፍረስ ተግባሩንም ለመቀልበስ የከተማዋ ነዋሪዎች ከጸጥታ ኀይሎች ጎን መሆናቸውን ለማሳየት፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙሪ የውኃ ሙሌትና የስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቅን በማስመልከት ድጋፍን ለመግለጽ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በአሁኑ ሰዓትም የከተማዋ ነዋሪዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እና የተለያዩ አሸባሪውን ቡድን የሚያወግዙ መፈክሮችን በመያዝ ወደ መስቀል አደባባይ እያመሩ ነው።
የድጋፍ ሰልፈኞቹ ከሚያሰሟቸው መፈክሮች ውስጥ:-
• የመከላከያ ሰራዊታችን የልዓላዊነታችን ምልክት ነው
• ከጀግናው መከላከያ ሠራዊት ጎን ነን
• የትህነግ ጁንታ ቡድን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠላት ነው
• የአብሮነት ጉዟችን በሽብርተኞች አይደናቀፍም
• ሰለማችን በአንድነታቸን ይጠበቃል
• ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚከፈል ዋጋ ከቡር ነው
• ኢትዮጵያ ላይ የሚውራረድ ሂሳብ የለም
• ኢትዮጵያ በጀግኖቿ አፍራ አታውቀም
• ክብር ለጀግ ናው መከላከያ ሠራዊታችን የሚሉት ይገኛሉ
ሰላማዊ ሰልፉ እስከ እኩለ ቀን የሚካሄድ ነው።


ዘጋቢ:–ዘመኑ ታደለ –ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ