
በአፋር ክልል በኩል ትንኮሳ የፈጸመው የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ተደመሰሰ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአሸባሪው ህወሓት ጁንታ “ሜይዴይ” በሚል ሰይሞ በአፋር ክልል አለሌ ሱሉላ በሚባል አካባቢ ያሰማራው ቡድን የሽብር ጥቃት በመፈጸሙ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የአስታወቀ።
የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ እንደገለጹት፤ የአሸባሪው ህወሓት ጁንታ በቆቦም በተመሳሳይ የሽብር ቡድን አሰማርቶ ጥቃት ሰንዝሮ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በወሰደው የመከላከል እርምጃ ቡድኑ መደምሰሱን እና ለውጊያ ያሰማራቸው በርካታ ህጻናት መማረካቸውን ኮሎኔል ጌትነት ተናግረዋል።
መንግሥት ለትግራይ ሕዝብ በማሰብ የወሰደውን የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ አሸባሪው ሕወሓት የሽብር ተግባር ለመፈጸም እንደመልካም አጋጣሚ እንደወሰደው ጠቅሰው፤ ቡድኑ ደግሞ ትንኮሳ ከፈጸመ የመከላከል እርምጃው እንደሚወሰድበት አረጋግጠዋል።
የአሸባሪው ትህነግ ትንኮሳ ያለማቆሙን በማየት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት መንግሥት ትዕዛዝ ከሰጠ በቡድኑ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ለማጥፋት ሠራዊቱ ዝግጁ መሆኑንም ኮሎኔል ጌትነት ለኢዜአ አስታውቀዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m