“በሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የተጎዱ የሠራዊት አባላት ለጀግንነታቸው የሚመጥን ክብካቤና ድጋፍ እንዲያገኙ እየሠራን ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

132
“በሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የተጎዱ የሠራዊት አባላት ለጀግንነታቸው የሚመጥን ክብካቤና ድጋፍ እንዲያገኙ እየሠራን ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) “በሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የተጎዱ የሠራዊት አባላት ለጀግንነታቸው የሚመጥን ክብካቤና ድጋፍ እንዲያገኙ እየሠራን ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ገለጹ።
“ጀግናው ሠራዊታችን የሀገራችንን ክብር፣ ነጻነት እና ሉዓላዊነት የሚያስከብረው የላብና የደም ዋጋ ከፍሎ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ገለጹ።
ይሄንን ተመን የማይገኝለት ዋጋ ሲከፍል ደግሞ ሕዝብ እና መንግሥት ከጎኑ መቆም እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።
“ድል ያለ መሥዋዕትነት አይገኝም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “እንደ ወታደር ዓለሚቱ አምባ ያሉ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የተጎዱ የሠራዊት አባላት ለጀግንነታቸው የሚመጥን ክብካቤና ድጋፍ እንዲያገኙ እየሠራን ነው” ብለዋል።
የሕክምናና የሰው ሠራሽ አካል ድጋፍ ማድረጊያ ማዕከላትን የማጠናከር ስራ እየተሰራ እንደሆነም ገልጸው፤ “ማኅበራዊ ሕይወታቸውን ለመደገፍ የሚያስችል ሥራም እየሠራን ነው” ብለዋል።
“ኢትዮጵያ ለእነርሱ የማትሆነው የለም” ሲሉም ገልጸዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንግሥት እና የስድስት ከተሞችን ፖርታሎች አልምቶ ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረጉን ገለጸ፡፡
Next articleብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ሆኑ።