የአዲስ አበባ ሕዝብ ጁንታውን በመቃወም በነገው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ ተገለጸ።

186

የአዲስ አበባ ሕዝብ ጁንታውን በመቃወም በነገው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ ተገለጸ።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ሕዝብ የሕወሓት ጁንታን በመቃወም በነገው ዕለት (ሐምሌ 15/2013 ዓ.ም) በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

ሰላማዊ ሰልፉ ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ እስከ አጋማሽ ቀን የሚካሄድ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አብዲ ፀጋዬ ገልጸዋል።

ሰልፉ የሕዝቡን ጥያቄ መሠረት በማደረግ የሚካሄድ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ የሰልፉ ዓላማ ጁንታውን ከመቃወም ባለፈ ሕዝቡ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያለውን ደጀንነት ለመግለጽ ነው ብለዋል።

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁ እና የሕዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት መከናወኑን ጨምሮ እስካሁን በሀገር ደረጃ የተገኙ ድሎች የሚወደሱበት መሆኑንም የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አብዲ ፀጋዬ ተናግረዋል። ኢብኮ እንደዘገበው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበጎንደር ከተማ የሚገኘው የአምባጅኔ አብሮ አደግ መረዳጃ አንድነት ማኅበር በህልውና ዘመቻ ለተሰማሩ የጸጥታ ኃይሎች አጋርነት የደም ልገሳ መርኃግብር አካሄደ።
Next articleየአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ለተለያዩ ጄኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የሥራ ምደባ ሰጡ።