
የህልውና ዘመቻዉን ውጤታማ ለማድረግ ያላሰለሰ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረሲና ከተማ አሚኮ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ባሕር ዳር: ሐምሌ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በተባበረ ክንድ ኢትዮጵያውያን ሽብርተኛው ትህነግን ለመደምሰስ ከመቸውም ጊዜ በላይ ሕብረት ፈጥረዋል፡፡
በደብረሲና ከተማ በበቆሎ መሸጥ ሥራ የተሰማሩት ወይዘሮ ትርንጎ ከበደ ለአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት በሶና ቆሎ ከማዘጋጀት ጀምሮ የ7 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ነው የገለጹት።
የሽብርተኛው ትህነግ አከርካሪ ተሰብሮ ግብዓተ-መሬቱ እስኪፈጸም ድረስ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ሌላው በሱቅ ንግድ ሥራ የተሰማሩት አቶ ስንታየሁ አለባቸዉ የጁንታዉን ቡድን ለመደምሰስ የሚደረገዉ ዘመቻ ውጤታማ ለማድረግ 10 ሺህ ብር መስጠታቸውን ነግረውናል።
በከተማዋ በሆቴል ሥራ የተሰማሩት አቶ መኩሪያ ተገኝ ለህልዉና ማስከበር ዘመቻዉ ከ30 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን ነው የገለጹት።
የጣርማ በር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሺዳኛ ፈቄ ኅብረተሰቡ የህልውና ዘመቻውን በመደገፍ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ወረዳው ለዚህ ዓላማ ከመንግሥት ሠራተኛዉና ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታውቀዋል።
ዘጋቢ:- ሀብታሙ ዳኛቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ