
“አሸባሪው ሕወሓት በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የቃጣውን ጥቃት እንደዚህ ቀደሙ በጋራ በመቆም ማክሸፍ ይገባል” የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተመሥገን ጥሩነህ
ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተመሥገን ጥሩነህና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጎንደር ከተማ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫው አቶ ተመሥገን እንዳሉት አሸባሪው ሕወሓት ጦርነቱ ከአማራ ጋር ብቻ በማስመሰል ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ጥረት እያደረገ ነው፡፡
ጦርነቱ ከአማራ ሕዝብ ጋር እያስመሰለው የሚገኘው ራሱ ጁንታው ነው ያሉት አቶ ተመሥገን ይህ የከፋፍለህ ግዛ ሐሳብ አሸባሪው ቡድን የኖረበትና ኢትዮጵያን ለመከፋፋል የሚጠቀምበት ነውም ብለዋል።
አሸባሪው ቡድን በአንድ በኩል ችግሬ ከአማራ ሊሂቃን ጋር ነው ቢልም በአፋር ክልል ላይ የፈጸመው ጥቃት የአሸባሪ ቡድንን ኢትዮጵያን የማጥቃት ዓላማውን በግልጽ የሚያመላክት መሆኑንም ገልጸዋል።
አሸባሪ ቡድኑ ከአማራ በመውረድ ሒሳብ የማወራርደው ከጎንደር ጋር ነው የሚል ሐሳብን የሚያረምደው ኢትዮጵያውያንን ከፋፍሎ ለማጥቃት መሆኑን በመረዳት ከዚህ ቀደም እንደታየው አንድነትን በመጠበቅ ዓላማውን ማክሸፍ ይገባልም ነው ያሉት።
የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ አንድነታችን በማስጠበቅ ብዙ ፈተናዎችን አልፈናል ብለዋል። አባቶቻቸን ኢትዮጵያ ፈተና በወደቀችበት ወቅት በአንድነት በመቆም የከፈሉትን መስዋእትነት በመክፈል በሀገር ላይ የተቃጣውን አደጋ መመከት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።
አሸባሪው ሕወሓት ሃይማኖት ከሃይማኖት ብሔርን ከብሔር በመከፋፈል ዓላማውን ለማሳካት መጣሩ የማይቀር ቢሆንም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደአባቶቻቸን በጋራ በመቆም እና መስዋእትነት በመክፈል ሀገራችንን እንስቀጥላለን ብለዋል።
ጠላት የሚነዛቸውን አሉባልታዎች ወደኋላ በመተው የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ በመሻገር ኢትዮጵያን ማስቀጠል ይገባል ማለታቸውን የዘገበው ፋብኮ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m