በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመተከል ዞን ተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ።

238

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመተከል ዞን ተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 13/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት የጋራ ግብር ኃይል ወደ መተከል ዞን የተመለሱ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

በአሜሪካ የምትኖረው ወይዘሪት ቅድስት ዘውዱ እና ጓደኞቿ በጋራ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር በተሰበሰበው ሀብት ለመተከል ዞን ተፈናቃዮች ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ድጋፉንም የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ካሡ ኃይሉ፣ እርቂሁን ዓለምነህና መብራቱ ይግዛው በማንዱራ ወረዳ በመገኘት አስረክበዋል፡፡May be an image of 5 people and people standing

ተወካዮቹ ድጋፉ በቀጣይ ጊዜያት ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ማቋቋም እሰከሚቻል ደረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አጀበ ሰንሻው እና የመተከል ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ፀሐይ ጉዮ ምስጋና አቅርበዋል። የሚደረገው ድጋፍ በመንግሥት አቅም ብቻ የሚመለስ ባለመሆኑ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከአማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የማንዱራ ወረዳ ዞን ተፈናቃዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ አባል አቶ አብዮት ጥላሁን ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m

Previous articleኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል እና ዓለም አቀፋዊ ድባቡ
Next article“አሸባሪው ሕወሓት በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የቃጣውን ጥቃት እንደዚህ ቀደሙ በጋራ በመቆም ማክሸፍ ይገባል” የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተመሥገን ጥሩነህ