
የ1ሺ 442ኛው የኢድ አዳ አል(አረፋ) በዓል በገንዳውኃ ከተማ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 13/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በዓሉ በተክቢራ ተጀምሮ በጸሎት ተጠናቋል። በበዓሉ ለህልውና ዘመቻው የወጡ ወንድሞች፣ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻና የሀገር መከላከያ ሠራዊት ድል አድርገው በሰላም እንዲመለሱ ጸሎት ተደርጓል።
ለ16 የግንባር ዘማች ቤተሰቦች ከ20 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የፍየል፣ የሽንኩርትና የዘይት ድጋፍ በማድረግም በዓሉ ተከብሯል።
በበዓሉ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የአካባቢውን ሰላም በጋራ እንዲጠብቅ የታላቁ ዑመር መስጊድ ኢማም ሼህ ሙሐመድ አብዱልቃድር አሳስበዋል።


የመተማ ወረዳ እስልምና ጉዳዮች ሊቀመንበር ሼህ ሑሴን አህመድ በዓሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት የተጠናቀቀበት ታሪካዊ ቀን በመሆኑ የበለጠ ደስተኛ ነን ብለዋል።
ሼህ ሑሴን አክለውም የውኃ ሙሌቱ መጠናቀቅ የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችንን የመመከት አቅም እንዳለን አንድ ማሳያ ነውና ድጋፉም ይቀጥላል ነው ያሉት።
በመላው ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የህዳሴ ግድቡ የውኃ ሙሌት መጠናቀቅ ደስታን እንደፈጠረና ለማገዝም ዝግጁ እንደሆኑ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡– ቴዎድሮስ ደሴ– ከገንዳ ውኃ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
