
“የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሁለተኛ ዙር ሙሌቱን ተከትሎ በዳያስፖራ ልገሳው ቀጥሏል” አምባሳደር ፍጹም አረጋ
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 13/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሁለተኛ ዙር ሙሌቱን ተከትሎ በዳያስፖራ ልገሳው ቀጥሏል፡፡
በዚህም ፡-
– ከዳላስ ቴክሳስ የደብረ-መንክርት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን 7 ሽህ ዶላር
– “1 ጡብ ለትውልድ” በሚል 11 ለጋሽች በድምሩ 6 ሽህ 200 በፓስተር ወርቁ ለገሰ አሰባሳቢነት
– የ’ZTruck’ ድርጅት ባለቤት 2 ሽህ ዶላር
– ዘውድነሽ አድማሱ 1 ሽህ ዶላር እና
– ሐሰን በሽር 1 ሽህ ዶላር መለገሳቸው ተመልክቷል፡፡
ለግድቡ ድጋፍ ያደረጉ አካላት ቼክ ማስረከባቸውን አምባሰደሩ በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አመላክተዋል፡፡ ለተደረገው ድጋፍ አምባሳደር ፍጹም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
